← ዜናዎች
event

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የፕላን እና ልማት ቢሮ ሥልጣንና ተግባራት

በሌሎች ሕጎች አስቀድሞ የተደነገገው ወይም ወደ ፊት የሚደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የክልሉ
የፕላን እና ልማት ቢሮ የሚከተሉት ዝርዝር ሥልጣን እና ተግባራት ይኖሩታል፡-
1/ የልማት፣ የክልላዊ ስታቲስቲክስ እና የሥነ ሕዝብ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ፖሊሲዎችን፣
ስትራቴጂዎችን እና ሕጎችን ያመነጫል፣ ለአፈፃፀሙ ከክልሉ የልማት አቅጣጫዎች ጋር
የተጣጣመ ዝርዝር መርሃ ግብር ያዘጋጃል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
2/ በክልሉ ተቋማት የሚመነጩ የልማት ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ከክልሉ የልማት
አቅጣጫዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
3/ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ልማት ፖሊሲ ጥናት እና ትንተና ያካሂዳል፣ በሚገኙ ውጤቶች
መሠረት ስትራቴጂያዊ የሶሾ ኢኮኖሚ ጉዳዮችን ይለያል፣ የፖሊሲ ምክረ ኃሳብ ያቀርባል፤
4/ የክልሉን የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ የልማት ዕቅዶች ለማዘጋጀት የሚረዱ
የኢኮኖሚ ጥናት እና ምርምሮችን ያካሂዳል፣ የኢኮኖሚያዊ እና የማህበራዊ ሁኔታዎች
መለኪያዎችን እና መመዘኛዎችን ያዘጋጃል፤

ተዛማጅ ዜናዎች